Fana: At a Speed of Life!

ማስተርካርድ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተጎዱ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ሊደግፍ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ማስተርካርድ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለተጎዱ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል።

ማስተር ካርድ ፋውዴሽን ከኢትዮጵያ ስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን እና ፈርስት ኮንሰልት አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው የድጋፍ ፕሮግራሙን ይፋ ያደረገው።

የአስቸኳይ የድጋፍ ፕሮግራሙም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑም ከማስተር ካርድ ፋውዴሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለድጋፉም በማስተር ካርድ ፋውዴሽን አማካኝነት የ24 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መነሻ ገንዘብ የቀረበ ሲሆን፥ ድጋፉም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ጠንካራ ሆነው ሰራተኞቻቸውን ይዘው እንዲቆዩ እንዲሁም ከወረርሽኙ በኋላ ፈጠራ የታከለበት የስራ እድል እንዲፈጥሩ የሚያስችል ነው ተብሏል።

የገንዘብ ድጋፉ ቀላል ብድርን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ተፈፃሚ የሚደረግ ሲሆን፥ የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ አይነት እና መጠንም እንደ ኢንተርፕራይዞቹ አቅም እና ፍላጎት የሚወሰን መሆኑም ተገልጿል።

የማስተር ካርድ ፋውዴሽን ድጋፍ 24 ሺህ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለገንዘብ ችግር እና ለመዘጋት አደጋ እንዳይጋለጡ የሚያስችል ሲሆን፥ 50 ሺህ ያክል ሰራተኞችም ስራቸውን እንዳያጡ ያስችላል ተብሏል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.