Fana: At a Speed of Life!

ማንኮራፋት አለማንኮራፋቱን ለማረጋገጥ እንቅልፉን በኢንተርኔት ያስተላለፈው ቻይናዊ ታዋቂ ሆኗል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በመኝታ ወቅት ማንኮራፋትና አለማንኮራፋቱን ለማረጋጋጥ በሚል እንቅልፉን በቀጥታ የኢንተርኔት ስርጭት ለተከታዮቹ ያደረሰው ቻይናዊ ወጣት ታዋቂነቱን አሳድጓል።

ወጣቱ በመኝታ ወቅት ማንኮራፋቱን ለማረጋገጥ በሚል ነበር እንቅልፉን ዶዩን በተሰኘው የቻይና ማህበራዊ ትስስር ገጽ ለተከታዮቹ በቀጥታ የኢንተርኔት ስርጭት ያደረሰው።

ይህን ተከትሎም የቀጥታ ስርጭት ተከታዮቹ ቁጥር በእጅጉ ሲጨምር፥ የተመልካቾቹ ቁጥርም ከ18 ሚሊየን በላይ ደርሷል ነው የተባለው።

የቀጥታ ስርጭቱን በሚገርም ሁኔታ በ100 ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች መመልከታቸው ነው የተገለጸው።

ከዚህ ባለፈም በቀጥታ ስርጭቱ ወቅት ግለሰቡ ከ800 ሺህ በላይ አዳዲስ ተከታዮች ማፍራት መቻሉ ተመላክቷል።

ያላሰበው ድርጊት ያመጣለት የተከታይና የተመልካች ቁጥር እንዳስደነገጠው ወጣቱ ገልጿል።

የቀጥታ የእንቅልፍ ስርጭቱ ለወጣቱ 76 ሺህ ዩዋን በማስገኘት ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝም ረድቶታል ነው የተባለው።

በርካቶች ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ቤት ውስጥ ለመዋል መገደዳቸውና የሚያዝናናቸው ነገር ፍለጋ ኢንተርኔት ላይ መዋላቸው፥ ለተከታዮቹም ሆነ ለተመልካቾቹ ቁጥር መጨመር የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለውም የመረጃው ምንጭ አመላክቷል።

ምንጭ፡-ኦዲቲ ሴንትራል

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.