Fana: At a Speed of Life!

ማይክሮሶፍት ለዊንዶውስ-10 ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚያቀርበውን የደህንነት መጠገኛ ለማቆም ማስቡን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ማይክሮሶፍት ለዊንዶውስ-10 የሚያቀርብውን የደህንነት ጥገና በ2025 ማቅረብ እንደሚያቆም እና በዚህ ወር መጨረሻ የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ዋና ማሻሻያ ይፋ ለማድረግ መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

ኩባንያው ከዚህ ቀደም ዊንዶውስ 10 ማሻሻያ ይፋ ሲያደርግ የመጨረሻው ኦፕሬቲንግ ሲስተም  ነው ቢልም አሁን ላይ ግን ሃሳቡን እንደቀየረ ይፋ አድርጓል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ኩባንያው ከፈረንጆቹ ጥቅምት 14 ቀን 2025 ጀምሮ ለሆምም  ሆነ ለፕሮፌሽናል ቨርዥኖች አዳዲስ ዝመናዎች ወይም የደህንነት ጥገናዎች አይኖሩም ብሏል፡፡

ምንም እንኳን የዊንዶው-7 ተጠቃሚዎች ከፈረንጆቹ 2020 ወዲህ የደህንነት ዝመና ቢቋረጥም የንግድ ድርጅቶች ለዊንዶውስ-7 ፕሮፌሽናል እና ዊንዶውስ 7 ኢንተርፕራይዝ ዝመናዎችን ለማግኘት ለማይክሮሶፍት ክፍያ እየፈጸሙ ነው።

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደተናገሩት አዲሱ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከ11 ቁጥር ይልቅ ስም እንደሚሰጠው እየገለጹ መሆኑን ቢቢሲ በድረ-ገጹ ማስነበቡን ኢመደኤ ዘግቧል።ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.