Fana: At a Speed of Life!

ማይክ ፖምፔዮ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ በኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት ቀናት ያካሄዱትን ጉብኝት አጠናቀቁ።

ማይክ ፖምፔዮ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ሲመለሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፈያ ተገኝተው አሸኛኘት አድርገውላቸውል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ከጠቅላይ ሚኒስርትር ዐቢይ አሕመድ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ሙሳፋቂ ማህማት እና ከልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የማይክ ፖምፔዮን ጉብኝት አስመልክቶ ባወጣው ሪፓርት ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ የኢኖሚያ አማራጭን ለማስፋት፣ ለንግድ ምቹ አካባቢን ለመፍጠር እና የስራ እድል ፈጠራን ለማበረታታት አሜሪካ 117 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጓን ይፋ አድርጓል።

እንዲሁም ሀገሪቱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን ለውጥ እየደገፈች እንደምትገኝ በመግለፅ በቀጣይ የሚካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ ለመደገፍ 37 ሚሊየን ዶላር ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ድጋፍ መደረጉም ነው የተጠቆመው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.