Fana: At a Speed of Life!

ምርት ገበያው ባለፉት አራት ወራት ከ51 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶችን አገበያየ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አራት ወራት ከ51 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የግብርና ምርቶችን በ4 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ማገበያየቱን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አስታወቀ፡፡
ከዚህ ውስጥ 17 ሺህ 690 ቶን ቡና፣ 15 ሺህ 445 ቶን ሰሊጥ፣ 3 ሺህ 24 ቶን ነጭ ቦሎቄ፣ 4 ሺህ 731 ቶን አኩሪ አተር፣ 3 ሺህ 368 ቶን አረንጓዴ ማሾ፣ 1 ሺህ 904 ቶን ዥንጉርጉር ቦሎቄ፣ 215 ቶን ቀይ ቦሎቄና አምስት ቶን የርግብ አተር አገበያይቷል።
በሐምሌ 2013 ዓ.ም የአንድ ኩንታል አማካይ የግብይት ዋጋ 7 ሺህ 235 ብር የነበረ ሲሆን÷ በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም 7 ሺህ 841 ብር ሆኗል ተብሏል፡፡
ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ዋጋው በእጥፍ ጨምሯል።
በሌላ በኩል ጥቁር አዝሙድ፣ ድንብላል፣ አብሽና ቁንዶ በርበሬ እንዲሁም ጓያ ወደ ዘመናዊ የግብይት ሥርዓቱ ስለተካተቱ ከያዝነው የምርት ዘመን አንስቶ ግብይታቸው እንደሚካሄድ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.