Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ አሽባሪው የሸኔ ቡድን በምእራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን አደጋ በፅኑ አወገዘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሽባሪው የሸኔ ቡድን በምእራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን አደጋ በፅኑ አወገዘ።

አሽባሪው የሸኔ ቡድን በጸጥታ ሀይሎች በከፍተኛ ሁኔታ ጥቃት እየደረሰበት በመሆኑ ከጥቃቱ በመሸሽም በምእራብ ወለጋ ንጹሀን ዜጎች ላይ አደጋ ማድረሱን ጠቅሷል።

በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ንጹሀን ዜጎቻችን ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ በእጅጉ የሚወገዝ መሆኑን ምክር ቤቱ ገልጿል።

“በዜጎቻችን ላይ በደረሰው ስቃይ እና መከራ እያዘንን ይሄንን አሸባሪ ቡድን ለማስወገድ መላው ህዝባችን በተለይም የአካባቢው ማህበረሰብ ከጸጥታ ሀይላችን ጋር በመተባበር እስከመጨረሻው እንድናስወግደው ጥሪ አቀርባለሁ ብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.