Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች በትርፍ ጊዜያቸው ስራቸውን እንዲያከናውኑ በሚል የቀረበውን የረቂቅ አዋጅ አንቀፅ ተቃወመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች በትርፍ ጊዜያቸው ስራቸውን እንዲያከናውኑ በሚል የቀረበውን የረቂቅ አዋጅ አንቀፅ ተቃወመ።

ምክር ቤቱ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ከህግ ፍትህና ዲሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ የቀረበውን ሀሳብ አዳምጧል።

በዚህም በረቂቅ አዋጁ አንቀፅ 18 ንዑስ አንቀፅ 2 የሰብአዊ መብት ኮሚሽነሮች ስራቸውን በትርፍ ጊዜያቸው ያከናውኑ የሚለውን ሀሳብ ተቃውሟል።

የሰብአዊ መብት ጉዳይ አንገብጋቢ ነው ያሉት አባላቱ፤ ስራው በሙሉ ጊዜ እንጂ በትርፍ ጊዜ ሊሰራ እንደማይችል አሳስበዋል።

በዚህ ምክንያትም ምክር ቤቱ አንቀፁ እንዲሻሻል በማድረግ ረቂቅ አዋጁ እንዲፀድቀ የውሳኔ ሀሳብ አስተላልፏል።

ምክር ቤቱ በዛሬው እለት የ2012 በጀት አመት ሪፖርቱ ላይ ከአባላቱ ጋር ውይይት አካሂዷል።

በተያያዘ ዜና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በበጀት አመቱ 58 ረቂቅ አዋጆችን  ማፅደቁን አስታወቀ።

ምክር ቤቱ የ2012 በጀት አመቱን በተመለከተ ለአባላቱ ባቀረበው ሪፖርት÷በበጀት ዓመቱ ከጸደቁት 58 አዋጆች በተጨማሪ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በጋራ 12 የውሳኔ ሀሳቦችን ማፅደቁም ተጠቅሷል ።

ከዚያም ባለፈ የኮቪድ 19 ወረረሸኝ በምክር ቤቱ የእቅድ አፈፃፀም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳሳረፈ በሪፖርቱ  ተገልጿል።

በብስራት መለሰ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.