Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ቦታን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ የፊታችን ቅዳሜ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል ያለውን ቅድመ ዝግጅት በዓሉ በሚከበርበት ቦታ ተገኝተው ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ ላይ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ መለሰ አለሙም ተገኝተዋል።
ምክትል ከንቲባ ዋ በዚሁ ወቅት በዓሉ የሚከበርበት ቦታ በሚገባ መዘጋጀቱን ተመልክተናል ብለዋል።
የኢሬቻ በዓልን ስናከብር በዓለም ላይ ተከስቶ በርካታ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘውን የኮቪድ- 19 ጥንቃቄ መዘንጋት የለበትምም ነው ያሉት ።
አያይዘውም በዓሉ ለኮቪድ 19 ጥንቃቄ ማድረግ በሚያስችል መልኩ እንዲከበር ከአባገዳዎች ጋር በመሆን ዝግጅቱ መጠናቀቁን ተናግረዋል።
የመስቀል በዓልን ከህዝቡ ጋር በመሆን በጥንቃቄ ና በሰላም እንዲከበር መደረጉንም አስታውሰዋል።
የኢሬቻ በዓል ሲከበርም እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ህዝቡ ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በመሆን አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ምክትል ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ መለሰ አለሙ በበኩላቸው ÷ የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የአብሮነት፣ የፍቅርና የአንድነት በዓል እንደመሆኑ መልካም እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበር በየደረጃው የሚገኘው አመራር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል።
አያይዘውም ህዝቡም በዓሉ በሰላም እንዲከበር የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል የኮቪድ 19 በተከሰተበት ወቅት በመሆኑ ከሌላው ጊዜ በተለየ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም አንስተዋል።
በሃይማኖት ኢያሱ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.