Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የታቦት ማደሪያ ስፍራ አፀዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኝ የታቦት ማደሪያን ከተለያዩ እምነት ተከታይ አባቶችና ምእመናን ጋር በመሆን ፅዳት አከናውነዋል።
ምክትል ከንቲባዋ ፅዳቱን ዮሴፍ ቤተክርስቲያን አካባቢ በመገኘት ያከናወኑ ሲሆን “የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ ፋይዳው ባሻገር ማህበራዊ ጥቅሙም ትልቅ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የጥምቀት በዓል የኢትዮጵያዊያን ህብር የሚገለፅበት ልዩ ድምቀት መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የጋራ የፅዳት መርሃ ግብሩ ኢትዮጵያዊያን የተለያየ ሃይማኖት፣ ብሄርና ማንንት ቢኖራቸውም አንድ መሆናቸውን ያመላከተ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሃይማኖት አባቶቹም በወቅቱ ባስተላለፉት መልእክት “ለኢትዮጵያ አንድነትና ሰላም በጋራ መስራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ እንገኛለን” ብለዋል።
በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው ሰላምና ደህንነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.