Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በፕሮፌሰር መስፍን ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።
ፕሬዚዳንቷ በሀገራችን የፓለቲካ ምህዳር አንጋፋ ቦታ የነበራቸው ፣ ሃሳባቸውን ካለ ምንም ይሉኝታና ፍርሃት በመግለጽ የምናውቃቸው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለዩን በጣም አዝኛለሁ ብለዋል።
ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ በማለት ሀዘናቸውን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ገልፀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለጓደኞቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ ብለዋል።

በተመሳሳይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አንጋፋ ምሁር፣ ፖለቲከኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ዜና ዕረፍት በመስማቴ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን
እየገለፅኩ ለቤተሰባችውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን እመኛለሁ ብለዋል በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ።
ፕሮፌሰር መስፍን የሚናገሩትና የሚሠሩት ተመሳሳይ ስለሆነ በርግጥም አስተማሪ ነበሩ፣ የአቅም ሰው ስለነበሩ አደንቃቸዋለሁ ነው ያሉት።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.