Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን ከቤልጂየም አቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከቤልጂየም አቻቸው ሶፊ ዊልምስ ጋር ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና በሁለቱ ሃገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ በጋራ መክረዋል።

በትግራይ ክልል የተጀመረው ህግን የማስከበር እርምጃ የደረሰበትን ምዕራፍ እና ዝርዝር ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የቤልጂየም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶፊ ዊልምስ በበኩላቸው፥ በሃገሪቱ የተፈጠረውን ችግር ለመከላከል መንግሥት በሚያካሂደው ህግ የማስከበር ዘመቻ ለንፁሃን ዜጎች ተገቢ ጥንቃቄ በመስጠት ማከናወን ይገባል ብለዋል።

መንግሥት ህግ የማስከበር እርምጃውን ለዜጎች ሰብዓዊ ደህንነትና ድጋፍ ሲባል በጥንቃቄ እና በሃላፊነት እንደሚያጠናቀቅ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።

በመጨረሻ የሁለቱ ሃገሮች ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ተሻለ የትብብር ደረጃ ለማሳደግ በሁሉም መስኮች በትኩረት እንደሚሰሩ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.