Fana: At a Speed of Life!

ም/ር መስተዳድር ሙስጠፌ ባጃጅ ላይ 300 ሺህ ብር አግኝቶ ለባለቤቷ ለመለሰው ወጣት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ባጃጅ ላይ 300 ሺህ አግኝቶ ለመለሰው የጅግጅጋ ከተማ ወጣት ጉሌድና ምስጋና አቀረቡ።

በጅግጅጋ ከተማ የባጃጅ አሽከርካሪ የሆነው ወጣት በሚያሽከረክረው ባጃጅ ውስጥ 300 ሺህ ብር ጥላ ለወረደችው እናት ተመልሶ በመምጣት ያገኘውን ብር መልሶላታል፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ባለፉት ሁለት ቀናት ምስጋና ሲቀርብለት ቆይቷል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ወጣቱ ለሰራው ስራ እና ይህን ወጣት በጥሩ ስነ ምግባር ላሳደጉት እናቱ በዛሬው ዕለት ምስጋና አቅርበዋል።

የ20 ዓመቱ ወጣት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ትምህርቱን ሳይቀጥል ቆይቷል።

አሁን ላይም ወጣቱ በጎ ሰው ትምህርቱን እንዲቀጥል የሶማሌ ክልል ድጋፍ እንደሚያደርግ አቶ ሙስጠፌ ያስታወቁ ሲሆን ለቤሰቦቹም የተለያዩ ድጋፎች ተደርገዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.