Fana: At a Speed of Life!

ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮችና የከተማዋ ነዋሪዎች “ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን!”በሚል ደም ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ነዋሪዎች “ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን!”በሚል የደም ልገሳ አካሄዱ።
በዚህ ወቅት ምክትል ከንቲባዋ “ጥፋት እና ክህደት የፈጸመብንን የህውሓት ቡድን በመፋለም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ውድ ህይወቱን መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ላለው መከላከያ ሰራዊት ደማችንን በመለገስ አጋርነታችንን በተግባር ማሳየት አለብን” ብለዋል ።
በህወሓት ጁንታ ወንጀለኛ ቡድን አመራሮች ላይ የተጀመረው ህግን የማስከበር ዘመቻንም በድል እየተወጣ ለሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት፣ የአጎራባች ክልሎች ልዩ ሃይል እና የሚሊሻ አባላት የላቀ ድጋፍ እና ክብር መስጠት ይገባልም ነው ያሉት።
በዘመቻው ተሳትፎ በማድረግ ላይ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት፣ የአጎራባች ክልሎች ልዩ ሃይል እና የሚሊሻ አባላት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ መጀመሩንም ወይዘሮ አዳነች ገልጸዋል።
ህብረተሰቡም በየአካባቢው በተዘጋጁ የድጋፍ ማዕከላት በመገኘት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚችለውን ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ጥሪ ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.