Fana: At a Speed of Life!

ሞዛምቢክ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዘመቻ ዛሬ ትጀምራለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሞዛምቢክ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን በዘመቻ መልክ ዛሬ መስጠት ትጀምራለች፡፡
በዚህም የጤና ባለሙያዎች በሥራ ወቅት ለቫይረሱ ከፍተኛ ተጋላጭ በመሆናቸው ክትባቱን በቅድሚያ ይወስዳሉ ነው ተባለው፡፡
የሞዛምቢክ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሃገሪቱ ባለፈው ወር ከቻይና ከተቀበለችው 200 ሺህ ዶዝ ውስጥ 121 ሺህ 530 ክትባቶችን ማሰራጨቱን ገልጿል፡፡
እንዲሁም ዛሬ ተጨማሪ 484 ሺህ ክትባቶችን ትቀበላለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከእነዚህ ውስጥ 384 ሺህ ከኮቫክስ 100 ሺህ ደግሞ በህንድ የተሰጠ የኮቪሺልድ ክትባት እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡
በሞዛምቢክ እስካሁን 62 ሺህ 520 በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን 693 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፤ 46 ሺህ 421 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል ነው የተባለው፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.