Fana: At a Speed of Life!

ሠራዊቱ በህዳሴ ግድብ የግዳጅ ቀጣና ሰላም ለማረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝ የሜካናይዝድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በታላቁ ህዳሴ ግድብ የግዳጅ ቀጣና ሰላም ለማረጋገጥ ቀን ከሌት ግዳጁን እየተወጣ እንደሚገኝ የሜካናይዝድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ተናግረዋል።
ምክትል አዛዡ እንደገለጹት ሜካናይዝዱ ሰፋፊ ግዳጆችን በመፈጸም ከመተከል እስከ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ስምሪቱን በማጠናከር ፀረ ሽምቅ እና ደፈጣ ውጊያዎችን በማካሄድ ጭምር የቀጣናውን ሰላም በጀግንነት አረጋግጧል ነው ያሉት።
ሜካናይዝዱ በመተከል ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በስፍራው ተሰማርተው ከሚገኙ የፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ተልዕኮውን በስኬት እየፈፀመ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ምክትል አዛዡ “በፀረ ሰላም ኃይሎች መሠረተ ቢስ ሐሳብ ሳንገታ ሕብረ ብሔራዊነታችንን አጠናክረን በቀጣናው አስተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ ምን ጊዜም ዝግጁ ነን” ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.