Fana: At a Speed of Life!

ረጅም ሰዓት የሚቀመጡ እድሜያቸው የገፋ ሴቶች ለልብ ህመም እንደሚጋለጡ ጥናት አመላከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ረጅም ሰዓት የሚቀመጡና እድሜያቸው የገፋ ሴቶች ለልብ ሕመም እንደሚጋለጡ አንድ ጥናት አመላከተ።

በአሜሪካ የልብ ማህበር የተጠናው አዲስ ጥናት አብዝተው የመቀመጥ ልምድ ያላቸው እና እድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ የሆናቸው ሴቶች ጤናማ ላልሆነ ከመጠን በላይ ውፍረት መዳረጋቸውን ያመላክታል።

ጥናቱ በሁለት ምድብ ተከፍሎ 63 ዓመት እና ከዛ በላይ እድሜ ባላቸው 518 ሴቶች ላይ የተደረገ ነው።

በጥናቱ የሰዎቹን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ (ምን ያክል ተቀምጠው እንዳሳለፉና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዳደረጉ) የሚከታተል መሳሪያ ጥቅም ላይ ውሏል።

በዚህም ደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን በመለካት አጠቃላይ ክትትል ተደርጎላቸዋል።
ረዘም ላለ ጊዜ በመቀመጥ የሚያሳልፉት ሴቶችም ከልክ በላይ በሆነ ውፍረትና ተያያዥ ችግሮች ለሚከሰት የልብ በሽታ ተጋላጭ

መሆናቸውን አጥኝዎቹ ገልጸዋል።
አጥኝዎቹ ብዙ ጊዜ ተቀምጦ ከማሳለፍ የእግር ጉዞ ወይም ቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባም ይመክራሉ።

ምንጭ፦ medicalnewstoday.com/

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.