Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ “ሞስኮ በዩክሬን መፈንቅለ መንግስት እንዲካሄድ እያሴረች ነው” በሚል ብሪታኒያ ያወጣችውን ክስ አጣጣለች

አዲስ አበባ፣ጥር 15፣2014 (ኤፍ ቢሲ ) ሩሲያ በዩክሬን “ለሞስኮ ታዛዥ መንግስት ለመመስረት መፈንቅለ መንግስት እንዲፈፀም እያሴረች ነው” በሚል ብሪታኒያ የምታናፍሰውን መረጃ አጣጣለች።

የብሪታንያ መንግስት በትላንትናዉ እለት በለቀቀው ጋዜጣዊ መግለጫ፥ “ሞስኮ በዩክሬን መፈንቅለ መንግስት እንዲፈፀም በማድረግ አፍቃሪ ሩሲያ መንግስት እንዲመሠረት ትፈልጋለች” ሲል ይከሳል።

ይህን ውጀላንም ቢቢሲን ጨምሮ ዘ ጋርዲያንና ፋይናንሺያል ታይምስ የመሠሉ መገናኛ ብዙኋኗን በማስተባበር ማሰራጨቷን ሩሲያ ገልፃለች።

ይህ የተደራጀ በሀሰት መረጃ የተደገፈ ዘመቻም የአሜሪካ መንግስትን ያካተተ መሆኑንም ተጠቁሟል።

የብሪታኒያን ውንጀላ የጣጣለው የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣዉ መግለጫ ለንደን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የውሸት መረጃ ማሰራጨቱን እንዲያቆም አሳስስቧል።

ይህ የብሪታኒያ መረጃ አልባ ክስ ሆን ተብሎ በዩክሬን ያለውን ውጥረት ለማባበስ ያለመ መሆኑንም ሞስኮ መግለጿን አር ቲ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.