Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ ወሰን ወታዳሮቿን አሰማራች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሩሲያ በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ ወሰን ኮባኒ ወታዳሮቿን አሰማራች፡፡

ሩሲያ ወታደሮቿን በሰሜን ሶሪያ አዋሳኝ ያሰፈረችው ከቱርክ ጋር ባደረገችው ስምምነት መሰረት መሆኑ ተነግሯል፡፡

በዚህም ሩሲያ በትናትናው ዕለት ወታደሮቿን በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ ወሰን አካባቢ ኮባኒ ማሰማራት መጀመሯ ነው የተገለጸው፡፡

አሜሪካ ከሰሜን ሶሪያ ቀጠና ወታደሮቿን የማስወጣት ውሳኔ ተክትሎ ቱርክ በቀጠናው በኩርድ ተዋጊዎች በሚመራው የሶሪያ ዴሞክራቲክ ሃይሎች ይዞታ ስር መጠነ ሰፊ ጥቃት መክፈቷ ይታወሳል፡፡

በአሜሪካ አሸማጋይነት የኩርድ ታጣቂዎች ከቀጠናው እስኪወጡ ድረስ ቱርክ ለአምስት ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ ማድረጓም ይታወቃል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራም ቱሪክ ይህን የተኩስ አቁም ስምምነት እንድታራዝም መጠየቃቸውም ይነገራል፡፡

በዚህም የተኩስ አቁም ስምምነቱ ቋሚ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷ አሜሪካ በአንካራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳቷን ዘገባው ያስረዳል፡፡

ምንጭ፡- ሬውተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.