Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በዩክሬን 389 ኢላማዎች መምታቷን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በዩክሬን የሰሜን ምሥራቅ ክፍሎች እያካሄደች ባለው የማጥቃት ዘመቻ 389 ኢላማዎችን መምታቷን አስታውቃለች፡፡

በሰሜን ምሥራቅ የዩክሬን ግዛት ውስጥ ጦሯን እንደገና ማሰማራቷንም ነው ሩስያ የገለጸችው።

ዩክሬይን በበኩሏ በሰሜንና በምሥራቅ የአገሪቱ ክፍሎች እያጠቃ ያለውን የሩስያ ጦር ግስጋሴ ለመግታት ሰራዊቷ በመፋለም ላይ መሆኑን አስታውቃለች።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ በጥቃቱ 15 የጦር መሳሪያ ማከማቻ መጋዝኖችን እና የዩክሬን ወታደራዊ ካምፖችን ጨምሮ 35 ወታደራዊ ማዘዥያ ያቦታዎችን መምታቷን ነው የመታችው፡፡

የተተኮሱት ሚሳኤሎች የጥይት ማከማቻ እና የነዳጅ ማደያ ቦታዎችንም አውድመዋል ነው የተባለው፡፡

የሩሲያ አየር መቃወሚያ የዩክሬን አውሮፕላኖች ወደ ብራያንስክ ክልል እንዳይገቡ መከላከሉንም የሩሲያ የዜና ምንጮችን ጠቅሶ ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡

የዩክሬይን ሁለተኛ ከተማ የሆነችው ካርኪቭ እስካሁን በዩክሬይን ሰራዊት ቁጥጥር ሥር ብትሆንም በየዕለቱ በሩስያ ሰራዊት በከባድ መሳሪያ እየተደበደበች እንደምትገኝም ነው የተገለጸው።

በዛሬው ዕለት ብቻ በከተማዋ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ፥ በሌሎች የአምስት ስዋች ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማዋ ወታደራዊ ምንጮች ይፋ አድርገዋል።

በሌላ በኩል የመንግስታቱ ድርጅት ዛሬ 66ኛ ቀኑን በያዘው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በደቡባዊዋ የማሪዮፖል ከተማ የሚኖሩትን ጨምሮ በዩክሬን ውስጥ ካሉ የጦር ቀጠናዎች ሰላማዊ ሰዎችን የማስወጣት ስምምነት ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል።

ሩሲያ ደግሞ እስካሁን ድረስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከጦርነት ቀጠና ወጥተው ወደ አገሬ እንዲገቡ አድርጊያለሁ ብላለች።

የሩሲያ የጦር ኃይሎች በተቆጣጠሯቸው የዩክሬን አካባቢዎች ዘረፋ ፈጽመዋል ሲሉ የዩክሬን ባለስልጣናት መናገራቸውም ተዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.