Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ከፍተኛዉን የኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር አስመዘገበች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ሩሲያ ከፍተኛዉን የኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር ማስመዝገቧን አስታውቃለች፡፡
በትላንትናዉ ዕለት ብቻ ከ 1 ሺህ በላይ ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይዎታቸዉ ማለፉ ታዉቋል፡፡
ይህም ኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ጀምሮ በሃገሪቱ ከፍተኛዉ የኮሮና ቫይረስ ቁጥር መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ፡፡
የሀገሪቱን የኮሮና ቨይረስ ስርጭት በተመለከተ መረጃ የሚሰጠዉ ጎጎቭ ድረ ገፅ እንዳስታወቀዉ÷ በሀገሪቱ 31 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወስደዋል፡፡
በሀገሪቱ ያሉ የኮሮና ቫይረስ ገደቦች ዉስን መሆናቸዉ ለስርጭቱ ምክንያት መሆኑን ነዉ አል ጀዚራ በዘገባዉ ያስታወቀዉ፡፡
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የጤና ሚኒስትሩ ሚካሂል ሙራሽኮ እንደተናገሩት÷ ሥርጭቱን ለመግታት የክትባት ዘመቻዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
በሀገሪቱ እስካሁን በተደረጉ ምርምራዎች 7 ሚሊየን 958 ሺህ 384 ዜጎች በቫይረሱ ሲያዙ ÷ 222 ሺህ 315 ዜጎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በሚኪያስ አየለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.