Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ 10 የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከሞስኮ እንዲወጡ አዘዘች

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ 10 የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ሞስኮን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች፡፡

ሞስኮን ለቀው እንዲወጡ ከታዘዙት ዲፕሎማቶች በተጨማሪም ስምንት የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ሃገሯ እንዳይገቡም እገዳ ጥላለች፡፡

ወደ ሩሲያ እንዳይገቡ ክልከላ ከተጣለባቸው መካከል የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) ዳይሬክተር እና የሃገሪቱ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ይገኙበታል ነው የተባለው፡፡

የአሀኑ ውሳኔ ባለፈው ሃሙስ በአሜሪካ ለተወሰደው እርምጃ አፀፋዊ ምላሽ መሆኑ ታውቋል፡፡

የአሜሪካ እርምጃ ሩሲያ ባለፈው አመት ፈጽማዋለች ላለችው የ“ሶላር ዊንድስ” የበይነ መረብ ጥቃት እና በ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ነበራት ላለችው ጣልቃ ገብነት የተሰጠ ምላሽ መሆኑ ታውቋል፡፡

አሁን ላይ ሃገራቱ ያላቸው ግንኙነት እየሻከረ ሲሆን፥ ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸውም ይነገራል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ሩሲያ በሺዎች የሚቆጠር ሰራዊቷን ወደ ዩክሬን እያስጠጋች ሲሆን፥ አሜሪካም ግዙፍ የጦር መርከቦቿን ወደ ጥቁር ባህር እያስጠጋች መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.