Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ 12 ስኬታማ የኃይፐርሶኒክ ሚሳኤሎች ሙከራ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን የዚርኮን ኃይፐርሶኒክ ሚሳኤሎች በተከታታይ ለ12 ጊዜ በማስወንጨፍ ሀገራቸው ስኬታማ ሙከራ ማድረጓን ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን ከሀገሪቷ እንዲሁም ከሣይንሥ እና ትምህርት ምክር ቤቶች ጋር በጥምረት ባደረጉት ስብሰባ ላይ እንደገለጹት ÷ ሚሳኤሉ እጅግ ዘመናዊ እና ማንኛውንም የምድርም ሆነ የአየር ላይ ዒላማ መምታት የሚችል ነው፡፡

ፕሬዚዳንቱ ÷ ሙከራው እጅግ ስኬታማ እንደነበረ ገልጸው ለሀገራቸውም ትልቅ ኩነት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የሚሳኤሉን ንድፍ ለሠሩት፣ ላበለጸጉት እና በአጠቃላይ የኃይፐር ሶኒክ ሚሳኤሉን ስርዓት እውን ላደረጉት ኢንጂነሮች ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

የሚሳኤሉ መበልጸግ የሀገሪቷን የደኅንነት እና የመከላከያ ብቃት ለማሳደግ ዓላማ ያደረገ መሆኑን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.