Fana: At a Speed of Life!

ሩስያ ስዊፍትን ለመተካት ያዘጋጀችው የገንዘብ መላኪያ ስርዓት ለብሪክስ ሀገራት ዝግጁ ነው አለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩስያ በስዊፍት ምትክ ያዘጋጀችው አዲሱ የገንዘብ መላኪያ ስርዓቷ ለብሪክስ ሀገራት ዝግጁ መሆኑን ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን እንዳሉት፥ የብሪክስ አባል ሀገራት ማለትም ደቡብ አፍሪካ ፣ ብራዚል፣ ሕንድ እና ቻይና የፋይናንስ ተቋማት ከሀገራቸው የገንዘብ ማስተላለፊያ ስርዓት ጋር አስመልክተው መገናኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ፑቲን በብሪክስ የቢዝነስ ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ሞስኮ ዓለም አቀፍ የገንዘብ መላላኪያ ስርዓቶቿን አጋር ላለቻቸው እነዚህ ሀገራት አስተማማኝ አማራጮችን እያዘጋጀች ነው ብለዋል።

አክለውም ፥ የብሪክስ መገበያያ በሆነ ገንዘብ ዓለም አቀፍ ግምጃ ቤት ለማቋቋም ሂደት ላይ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

አዲሱ የገንዘብ ማስተላለፊያ ስርዓት ከስዊፍት ጋር ተመሳሳይ ተግባር እና በገንዘብ ተቋማት መካከል መልዕክቶችን በተመሳሳይ ማስተላለፍ የሚያስችል ነው ተብሏል።

አዲሱ የገንዘብ ማስተላለፊያ ስርዓት ሞስኮ ከዩክሬን ጋር እያካሄደችው ባለው ጦርነት ምክንያት በምዕራቡ ዓለም የተጣለባትን ማዕቀብ ለመቋቋም የተፈጠረ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

በሚያዝያ ወር ላይ የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ኤልቪራ ናቢሊና አብዛኞቹ የሩሲያ አበዳሪዎች እና ከ12 ሀገራት የመጡ 52 የውጭ ድርጅቶች አዲሱ የገንዘብ ማስተላለፊያ አገልግሎት ማግኘታቸውም ተነስቷል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም የክፍያ ስርዓቱ የአባላቱን ማንነት በሚስጥር ይጠብቃል ሲል የዘገበው አር ቲ ነው ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.