Fana: At a Speed of Life!

ሪያል ማድሪድ የስፔን ላ ሊጋ አሸናፊ መሆኑን አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሪያል ማድሪድ የዘንድሮው የስፔን ላ ሊጋ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ትናንት ምሽት የላ ሊጋው 37ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡

በሜዳው ቪያሪያልን ያስተናገደው ሪያል ማድሪድ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ይህን ተከትሎም ላ ሊጋውን ለ34ኛ ጊዜ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በሌላ በኩል ከኦሳሱና የተጫወተው ባርሴሎና 2 ለ 1 ሲሸነፍ ጌታፌን 2 ለ 0 ያሸነፈው አትሌቲኮ ማድሪድም የቀጣይ አመት የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን አረጋግጧል፡፡

ኤስፓኞል ደግሞ ከላ ሊጋው የወረደ የመጀመሪያው ቡድን ሆኗል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.