Fana: At a Speed of Life!

ራስን ከኮሮና ቫይረስ ለመጠበቅ መደረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) መነሻው ቻይና የሆነው የኮሮና ቫይረስ በተለያዩ የአለም ሀገራት ተሰራጭቶ 83 ሺህ ሰዎች ማጥቃቱ ተነግሯል።

ከዚህ ባለፈ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከ 2 ሺህ 788 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ነው
መረጃዎች የሚያመለክቱት።

በመሆኑም በአለም ላይ ከፍተኛ ስጋትን ከደቀነው ከዚህ ቫይረስ ራስን ለመጠበቅ የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል።

ጥንቃቄዎቹም፡-

1. በሕይዎት ካሉም ሆነ ከሞቱ የቤትና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ

2.ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ

3. የትኩሳትና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣

4. እጅን በሳሙናና ውሃ መታጠብ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም
ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ከፈጠሩ፣

እንዲሁም በበሽታው መያዛቸውን የጠረጠሩ ሰዎች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች ደግሞ÷

ወደ ሀገር በተመለሱ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ የመተንፈሻ አካል ህመም ፣ ትኩሳትና እንደሳል ያሉ የህመም ምልክቶች ካለብዎት ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት ማግኘት፣

የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አስራ አራት (14) ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገራት ሄደው ከነበረ ይህንንም ለጤና ባለሙያው ማስረዳት፤

በሚያስሉበትናበሚያስነጥሱበትጊዜበሽታውወደጤነኛሰውእንዳይተላለፍአፍናአፍንጫንበክንድ፣በመሃረብወይምበሶፍትመሽፈን፣

አፍና አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡

በሽታውን ሪፖርት ወደ አደረጉ ሀገራት ሄዶ የበሽታውን ምልከቶች ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቋም ማሳወቅ ወይም ከታች በተገለፁት አድራሻዎች በመጠቀም ሪፖርት ማድርግ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.