Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ ትልቅ የተባለውን ወታደራዊ ትዕይንት ልታሳይ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ በታሪኳ ትልቅ የተባለውን ወታደራዊ ትዕይንት ለማሳየት እየተዘጋጀች መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

ወታደራዊ ትዕይንቱ የሠራተኞች ፓርቲን 75ኛ ዓመት ምስረታን በማስመልከት የሚካሄድ ነው ተብሏል፡፡

ለአሁኑ ወታደራዊ ትዕይን ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ የተመረጡ ወታደሮች ሲለማመዱ እንደነበርም ተገልጿል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ሃገራት የትዕይንቱን ምንነት ለመረዳት የሳተላይት ምስሎችን እየተጠቀሙ ነው፡፡

አንዳንዶቹም ወታደራዊ ትዕይንቱን ፒዮንግያንግ አለኝ የምትለውን ወታደራዊ አቅም ለዓለም ለማሳየት የምታካሂደው መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

ከዚህ በተጫማሪም ሃይልን በማሳየት ለማስፈራሪያነት ለመጠቀም በማለም የሚካሄድ ሊሆን እንደሚችልም እየገለጹ ነው፡፡

በነገው ትዕይንት ላይ ሰሜን ኮሪያ ባላስቲክ ሚሳኤልን ጨምሮ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎቿን ልታሳይ ትችላለች ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ እና ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.