Fana: At a Speed of Life!

ሰው የያዘችው የመጀመሪያዋ የግል ኩባንያ ንብረት መንኮራኩር በአለም አቀፍ ጠፈር ጣቢያ ላይ አረፈች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በናሳ እና በስፔስ ኤክስ ጥምረት ወደ ህዋ የተላከችው መንኮራኩር በዛሬው ዕለት በአለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ ላይ አርፋለች።
 
በናሳ እና በግሉ የጠፈር ምርምር ኩባንያ ስፔስ ኤክስ ጥምረት ወደ ህዋ በትናትናው ዕለት የመጠቀችው መንኮራኩር ሁለት የአሜሪካ ህዋ ተመራማሪዎችን መያዟ ተነግሯል።
 
በዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ ላይ የደረሱት ሁለት ካፕቴኖች ዶግ ሃርሌይ እና ቦብ ቤኸንከን ናቸው።
 
የመንኳራኩሯ የስራ ሂደቷ ከሰው ንኪኪ ውጪ ራሱን በራሱ የሚያዝ አውቶማቲክ ሲሆን ግለሰቦቹ አንድንድ ስራዎች ብቻ መከወን ይጠበቅባቸዋል።
 
ይህ ተልዕኮም ናሳ ከህዋ ሳይንስ ጋር ለተያያዘ የትራስፖርት አገልግሎት ለግል የንግድ ተቋማት ክፍያ እንዲፈፀም ያደርጋል ነው የተባለው።
 
ከመንኮራኩሯ ጋር ወደ ህዋ የመጠቁት ተመራማሪዎቹ ለቀጣዮቹ 100 ቀናት ቆይታቸውን በጠፈር ላይ ያደርጋሉ ተብሏል።
 
ድራጎን የሚል መጠሪያ ስም የተሰጣት መንኮራኩሯ በስፔስ ኤክስ የተዘጋጀች በድጋሜ ጥቅም ላይ የምትውል የእቃ ማመላለሻ መሆኗ ተነግሯል።
 
ከአሜሪካ ምድር ሰው የያዘ መንኮራኩር ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ወደ ህዋ ሲመጥቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
 
ምንጭ፡- ቢቢሲ
 
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.