Fana: At a Speed of Life!

ሱር ኮንስትራክሽን ከመንገድ ስራ ወደ ምሽግ ቁፈራ ገብቶ እንደ ነበረ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሱር ኮንስትራክሽን የተሰጠውን የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ትቶ ወደ ምሽግ ቁፈራ ገብቶ እንደነበረ ተገለጸ።
በአማራ ክልል ዋግህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የበርገሌ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ሲሳይ ካሴ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ሱር ኮንስትራክሽን በክልሉ በኮንትራት ከያዘው የመንገድ ሥራ ወጥቶ በምሽግ ቁፈራ ሥራ ላይ ተሰማርቶ ነበረ።
በርገሌ ወረዳ አቅራቢያ የተቆፈረው ምሽግ እስከ 10 ኪሎሜትር እርዝመት 2 ሜትር ጥልቀት 4-5 ሜትር ስፋት እንዳለውና መኪኖች ገብተው መውጣት የሚችሉበት እንደነበረ ገልፀዋል።
መከላከያ ሰራዊት ባካሄደው የህግ ማስከበር እርምጃ ከሁለት ሳምንት በፊት በአጭር ሰዓት ምሽጉን ተቆጣጥሮ የአካባቢው ማህበረሰብ ወደ መንደራቸው እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ምክትል ኮማንደር ሲሳይ ካሴ ገልፀዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.