Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን እና ግብፅ ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት ሱዳን እና ግብፅ ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የሱዳን ጦርሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሙሃመድ አልሁሴን እና የግብጹ አቻቸው ሞሃመድ ፋሪድ ናቸው ካርቱም ላይ ስምምነቱን የደረሱት ተብሏል፡፡

ስምምነቱን ባኖሩበት ወቅት ሁለቱም ሃገራት ብሄራዊ የደህንነት ስጋት እንደተደቀነባቸው አስታውቀዋል፡፡

የሱዳኑ የጦርሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ስምምነቱ ከብሄራዊ የደህንነት ጉዳይ ባሻገር ልምድ ያለው ጦር ለመገንባት ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ግብጽ ለሱዳን ለምታደርገው ድጋፍም ጠቅላይ ኢታማዡር ሹሙ ምስጋነናአቅርበዋል፡፡

የግብጹ አቻቸው በበኩላቸው ሃገራቸው ከሱዳን ጋር በሁሉም መስኮች ትብብር ለማድረግ ማቀዷን ገልጸዋል፡፡

በተለይም በወታደራዊ እና በደህንነት ጉዳዮች ግንኙነቷን እንደምታጠናከርም አስረድተዋል፡፡

ምንጭ፡- ሺንዋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.