Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን የህክምና ባለሙያዎቿን ከጥቃት የሚጠብቅ የፖሊስ ኃይል ልታቋቁም ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን የህክምና ባለሙያዎቿን ከጥቃት ለመጠበቅ የፖሊስ ኃይል ልታቋቁም መሆኗን ገለጸች።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መባባሱን ተከትሎ በጤና አጠባበቅ ሰራተኞቿ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመከላከል የፖሊስ ሃይል ለማቋቋም በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ነው የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተናገረው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ከህክምና ባለሙያዎች ተወያይተዋል።

መንግስት ለህክምና ባለሙያዎች ጥበቃ ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ያወጣል ብሏል መግለጫው ።

ባለፉት ሁለት ወራት በመላ አገሪቱ በጤና አጠባበቅ ሠራተኞች እና ተቋማት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ተፈጽመዋል ያለው የሱዳን ዶክተሮች ኮሚቴ ነው።

ለአስርት አመታት በጦርነት እና እገዳ ውስጥ የነበረችው ሱዳን የጤና ስርዓቷም ደካማ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል፡፡

ምንጭ፦አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.