Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ይገባኛል ማለቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኮነነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን መንግስት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የግንባታ ስፍራ የሆነውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ይገባኛል ማለቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኮነነ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሳምንታዊ መግለጫቸውም የታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ በሱዳን በኩል የተጣረሱ መረጃዎች እየወጡ ነው ብለዋል።

በሱዳን በኩል ከዚህ በፊት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መግፋቷ ሳያንስ አሁን ደግሞ የታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተገነባ ያለበትን የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ይገባኛል ማለቷ ያልተገባ ተግባር ነው ብለውታል ቃል አቀባዩ።

የሶስቱን ሃገራት ድርድር በተመለከተ ኢትዮጵያ ባላት አቋም እንደጸናች መሆኗንም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ባሳለፍነው ሳምንት ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ለእስያ አምባሳደሮች በኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ በታላቁ ህዳሴ ግድብ እና በትግራይ ክልል እየተከናወነ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ረገድም የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል ነው የተባለው።

ስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫን በተመለከተ የሃገሪቱን የምርጫ ህግ ተከትሎ ነጻ ገለልተኛ ምርጫ እንዲሆን እየተሰራ ነው ብለዋል አምባሳደር ዲና።

የመራጮች ምዝገባም በጅማሬው ወቅት ካሳየው መቀዛቀዝ መውጣቱንም ጠቅሰዋል።

በምስክር ስናፍቅወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.