Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን ድንበሯን በተጠናከረ መንገድ እድትጠብቅ እንጂ የኢትዮጵያን መሬት እንድትይዝ ፈቃድ የሰጣት የለም- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል ያለው ውዝግብ በሰላምዊና በድርድር እንዲፈታ ኢትዮጵያ አሁንም ዝግጁ ናት ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ሱዳን በድንበር አካባቢ የምታደርገው እንቅስቃሴ የሀገሪቱ ህዝብ ፍላጎት አይደለም ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ህግን የማስከበር እርምጃ በትግራይ ክልል በጀመረበት ወቅት ሱዳን ድንበሯን በተጠናከረ ሁኔታ እንድትጠበቅ ኢትዮጵያ አሳስባ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

ሆኖም የሱዳን ጦር ድንበሩን ተሻግሮ የኢትዮጵያን መሬት ተቆጣጥሯል ያሉት ቃል አቀባዩ ይህንንም አንዳንድ የሱዳን ባለስልጣናት ደግፈዋል ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የሱዳን ወታደሮች ከገቡበት የኢትዮጵያ አካባቢ ለቀው እንዲወጡ እያሳሰበ መሆኑንም ገልፀዋል።

ነገር ግን አሁንም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የድንበር ጉዳይ ወደ ግጭት ለመውሰድ የሚንቀሳቀሱ አካላት መኖራቸውን አንስተዋል።

የታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተም የሶስትዮሽ ድርድር እንደሚቀጥል በመጥቀስ ግንባታውና ሙሌቱ እንደማይቋረጥም አስረድተዋል።

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ወቅት የውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነት አለ ተብሎ የተወራው ሀሰት መሆኑን አረጋግጠዋል።

በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጉዳይ በተመለከተም ለተለያዩ ሀገራት ገለጻ እየተደረገ መሆኑንም አውስተዋል።

በአዳነች አበበ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.