Fana: At a Speed of Life!

ሲንጋፖር ከእርድ እንስሳት ውጪ በቤተ ሙከራ ያደገን የዶሮ ስጋ ለምግብነት እንዲውል ወሰነች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሲንጋፖር በዓለም ላይ ከእርድ እንስሳት ውጪ በቤተ ሙከራ ያደገን የዶሮ ስጋ ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆነች።

ይህ ውሳኔም መቀመጫውን ሳን ፍራንሲስኮ ላደረገው ኢት ጀስት ኩባንያ በቤተ ሙከራ ያሳደጋቸውን ዶሮዎች ለሽያጭ እንዲያቀርብ መንገድ ከፍቷል ነው የተባለው።

በቤተ ሙከራ ያደገው የዶሮ ስጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዳቦ ጋር ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እንደሚውል የተገለፀ ሲሆን መቼ ለገበያ ይውላል የሚለውን ግን ኩባንያው እስከአሁን ያለው ነገር የለም።

ከጤና፣ ከእንስሳት ደህንነት እና ከአካባቢው ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ተጠቃሚዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ተከትሎ አማራጭ የስጋ ፍላጎቶች ከፍ እያሉ መሆኑ ተጠቁሟል።

በቀጣዮቹ አስር ዓመት አማራጭ የስጋ ምርቶች 140 ቢሊየን ዶላር እንደሚያንቀሳቅሱ ሲገመት ይህም ከ1 ነጥ 4 ትሪሊየን የስጋ ገበያ 10 በመቶውን የሚሸፍን መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው ላይ አስፍሯል።

በዓለም ከእፅዋት ፕሮቲን የሚዘጋጁ የስጋ አይነቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ በሱፐር ማርኬቶች የተለመዱ ቢሆንም በሲንጋፖር ጥቅም ላይ እንዲውል የተወሰነው የቤተ ሙከራ ስጋ ከእንሳስት የጡንቻ ሴሎች የሚዘጋጅ በመሆኑ የተለየ አድርጎታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.