Fana: At a Speed of Life!

ሲኖዶሱ ምዕመናን በየቤታቸው በፀሎት እንዲወሰኑ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ስርአተ ቅዳሴን ጨምሮ መንፈሳዊ አገልግሎት ከነገ ጀምሮ በተወሰኑ ካህናት እንዲሰጥ ውሳኔ አሳለፈ።

ሲኖዶሱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አገልግሎቱን ከሚሰጡት የተወሰኑ ካህናት ውጭ ሌሎች አገልጋዮች እና ምዕመናን በቤታቸው እንዲቆዩ መወሰኑን አስታውቋል።

በአገልግሎት ላይ ያሉ አገልጋይ ካህናትም በቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ እንዲወሰኑ ሆኖ አስፈላጊው ሰርክ ህብስት የምግብ አቅርቦት እንዲዘጋጅላቸውም ወስኗል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስር በመላው ሃገረ ስብከት የሚገኙ መንፈሳዊ ኮሌጆች፣ የካህናት ማሰልጠኛዎች፣ ዘመናዊ ትምህርት ቤቶች አስፈላጊው ዝግጅት እንዲደረግላቸውና መሟላት የሚገባቸው ሁሉ ተሟልተው ለህሙማን ማቆያ እንዲሆኑ ለማድረግ ወረርሽኙ እስከሚያበቃ ድረስ አገልግሎት መስጫ እንዲሆኑ የሚመለከተው አካል ተረክቦ እንዲያስተናግደውም ነው የወሰነው።

ቤተ ክርስቲያኗ የኮቪድ19 ስርጭትን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጓን ገልፃለች።

በመግለጫው ህብረተሰቡ በጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ ምክረ ሃሳቦችን እና መመሪያዎችን በአግባቡ እንዲተገብርም ጥሪ ቀርቧል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.