Fana: At a Speed of Life!

ሲዋጉና ሲያዋጉ የነበሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጁንታው ታጣቂ ሃይል ጋር በመሰለፍ ከመቀሌ እስከ ቆላ ተንቤን ሲዋጉና ሲያዋጉ የነበሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖች በመከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ጸጥታ ሃይሎች የጋራ አሰሳና ፍተሻ ስራ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከጁንታው የጥፋት ቡድን ጋር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተሰለፉ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለመንግስት እንዲሰጡም በድጋሚ ጥሪ ቀርቧል።

የመከላከያ ኢንዶክትርኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ለኢዜአ አንደገለጹት 18ቱ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉት የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ጸጥታ ተቋማት በቅንጅት ባካሄዱት አሰሳና ፍተሻ ነው።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መኮንኖች መካከል ዘጠኙ የሙሉ ኮሎኔል ማዕረግ፣ ሰባቱ የሌተናል ኮሎኔል ማዕረግ ያላቸውና ሁለቱ ደግሞ የፖሊስ ኮማንደሮች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሜጀር ጄኔራል መሃመድ፤ ወንጀለኞችን የማደኑ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉም  ገልፀዋል።

ከጁንታው የጥፋት ቡድን ጋር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተሰለፉ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለመንግስት እንዲሰጡም ሜጀር ጄኔራሉ በድጋሜ ጥሪ አቅርበዋል።

ህዝቡም ለፀጥታ ሃይሉ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉንም ተናግረዋል።

በቅርቡ ከጁንታው የጥፋት ቡድን ጋር ተሰልፈው ከነበሩት ከፍተኛ መኮንኖች መካከል ሜጀር ጄኔራል መሀመድ እሻን ጨምሮ ሌሎች የጁንታው ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እጃቸውን መስጠታቸው ይታወሳል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.