Fana: At a Speed of Life!

ሳምሰንግ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ አመት 6 ነጥብ 7 ሚሊየን 5ጂ ዘመናዊ ስልኮችን ሸጧል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳምሰንግ ኩባንያ በተጠናቀቀው የፈረንጆች ዓመት 6 ነጥብ 7 ሚሊየን አምስተኛ ትውልድ (5ጂ) ኢንተርኔት የሚጠቀሙ ዘመናዊ ስልኮችን ለደንበኞቹ ሸጧል።

ኩባንያው በዓመቱ 4 ሚሊየን 5ጂ ስማርት ስልኮችን ለመሸጥ አቅዶ 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ስልኮችን በተሳካ ሁኔታ መሸጡን አስታውቋል።

ይህን ተከትሎም ኩባንያው 5ጂ ኢንተርኔት የሚጠቀሙ ስልኮችን በደንበኞች እጅ በማድረስ ከተቀናቃኞቹ የተሻለው ሆኗል።

በዓመቱ ለገበያ ከቀረቡ ዘመናዊ ስልኮች ውስጥ ሳምሰንግ ኤስ ኤስ ኤን አል ኤፍ የተሰኘው ሞዴል ብባዛት መሸጡ ተመላክቷል።

እንዲሁም ሳምሰንግ ጋላክሲ ኖት 10ጂ፣ 10+5ጂ፣ ኤ90 5ጂ እና የመተጣጠፍ ችሎታ ያለው ጋላክሲ 5ጂ በዓመቱ ለገበያ የቀረቡ ሞዴሎች ናቸው።

ሳምሰንግ በአዲሱ የፈረንጆች ዓመትም ለኩባንያው የመጀመሪያ የሆነውን ኤስ6 የተሰኘ 5ጂ ኢንተርኔት የሚጠቀም ታብሌት ለገበያ እንደሚያቀርብ ገልጿል።

 

ምንጭ፦ ሲ ኤን ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.