Fana: At a Speed of Life!

ሴቪያ የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩሮፓ ሊግ ትናንት ምሽት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

በጀርመን ኮሎኝ የተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ የስፔኑን ሴቪያ ከጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ተገናኝተው ሴቪያ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል፡፡

በጨዋታው ኢንተር ሚላን በሮሜሉ ሉካኩ የፍጹም ቅጣት ምት ጎል ቀዳሚ መሆን ችሎ ነበር፡፡

ይሁን እንጅ ደ ዮንግ በተከታታይ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች እንዲሁም ሉካኩ በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠረው ጎል ሲቪያ ባለድል ሆኗል፡፡

ዲያጎ ጎዲን የኢንተር ሚላንን ሁለተኛ ጎል ቢያስቆጥርም ቡድኑን መታደግ አልቻለም፡፡

ድሉን ተከትሎም የስፔኑ ክለብ ዩሮፓ ሊግን ለስድስተኛ ጊዜ ጊዜ ማሳካት ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.