Fana: At a Speed of Life!

ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋገጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶክተር ስለሺ በቀለ ከሴናተር ጂም ኢንሆፍ ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል።

በውይይታቸው አምባሳደር ስለሺ ሴናተር ኢንሆፍ ለኢትዮጵያ እያደረጉ ያሉትን ድጋፍ አድንቀዋል፡፡

እንዲሁም በወቅታዊ የኢትዮጵያ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች እና መንግስት በሰሜኑ ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭትና በተፈጥሮ አዳጋ ለተጎዱ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ እያደረገ ስላለው ጥረት ገለጻ አድርገዋል።

በተጨማሪ አምባሳደሩ በአሜሪካ ኮንግረስ  የቀረበው  ኤችአር 6600 እና ኤስ-3199 ረቂቅ ህግ  ዙሪያ፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ ከአጎዋ  መታገዷ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው በተለይም በሴቶች ላይ ስላለው አሉታዊ ተጽእኖ ለሴናተሩ አብራርተዋል።

ሴናተር ጂም ኢንሆፍ  ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር የረጅም ጊዜ አጋር  መሆኗን ጠቅሰው  ረቂቅ ሕጎቹ ጠቃሚ አይደሉም ያሉ ሲሆን ÷በአጎዋ ዙሪያም ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም  በሁለቱ ሀገራት መካከል የበለጠ ውጤታማ ግንኙነት እንዲኖር ከአምባሳደሩ ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ ቃል  መግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.