Fana: At a Speed of Life!

“ስለኢትዮጵያ” መድረክ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀው 9ኛው “ስለኢትዮጵያ” መድረክ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የውይይት መድረኩ “ሚዲያ ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በመድረኩ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉን ጨምሮ፣ የፌዴራል መንግስትና የክልሉ የሥራ ሃላፊዎች፣ አንጋፋ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡
የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ÷ኢትዮጵያ በውድ ልጆቿ ጥረት በርካታ ፈተናዎችን አልፋ በከፍታ እየቀጠለች ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ሁለተኛ ተርባይን ስራ ማስጀመሯ እና ሶስተኛውን የውሃ ሙሌት በስኬት ማጠናቀቋን እንዲሁም የአረንጓዴ አሻራን በተሳካ መንገድ ማከናወኗን በማሳያነት አንስተዋል፡፡
ሚኒስትሩ የሀገርን ሰላም ያወኩ አጥፊ ሃይላት መስመር እንዲይዙ መደረጉን እና የተረጋጋ ኢኮኖሚ መፈጠሩንም አስረድተዋል፡፡
ዶክተር ለገሰ ሚዲያዎች ለሀገር ግንባታና ለብሄራዊ ጥቅም መከበር መስራት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በመድረኩ “ስለኢትዮጵያ መድረክ” ወቅታዊ የሀገሪቱን ፈተና ለመሻገር አማራጭ የመፍትሄ ሀሳቦች እየቀረቡበት መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.