Fana: At a Speed of Life!

ስለ ፋና

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ

ተቋማችን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በ1987 ዓመተ ምህረት ሲቋቋም በኃላ ቀር መሳሪያዎችና በጥቂት የሰው ሃይል በሀገራችን የብሮድካስት ሚዲያ አዲስ አቀራረብ ይዞ ወደ ስራ ገባ። በሂደትም አደረጃጀቱንና የፕሮግራም ይዘቱን እያሻሻለና ችግሮቹን እየቀረፈ ገስጋሴዉን ቀጠለ። ህብረተሰብ ተኮር ፕሮግራሞች ላይ በማጠንጠን የሚታወቀውና ለህዝባችን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ኑሮ መሻሻልና መዳበር የሚተጋው የሚዲያ ተቋማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ አድማጮቹን እና ተመልካቾቹን እንዲሁም ተባባሪዎቹን ያበረከተ በቴሌቪዥን፣ ሬዲዮና ኦንላይን ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ ተመራጭ እየሆነ መጥቷል።

ተቋማችን ራሱን በተማረ እና ልምድ ባካበተ የሰዉ ሃይል ያሟላና ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ያዋሃደ የማስተማር፣ የማሳወቅና የማዝናናት ሚናዉን አጠናክሮ በመቀጠል በሀገራችን ሚዲያ ለውጥ ማምጣቱን ቀጥሏል። በሬዲዮ እና በኦንላይን የሚዲያ ዘርፍ የረዥም ጊዜ ልምድን ያካበተው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሀገራችን ታሪክ ለሚዲያ ተብሎ የተሰራ ባለ 11 ፎቅ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ህንፃ ባለቤት በመሆን ከሀገራችን አልፎ በምስራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም የሚዲያ ተቋም የመሆን ህልሙን ለማሳካት ከጥር 2003 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አድጎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

ባስገነባው የሚዲያ ኮምፕሌክስ ሙሉ በሙሉ ኤች ዲ/HD/ የሆነ የቴሌቪዥን ስቱዲዮ በመገንባትም በሀገሪቱ ታሪክ ሙሉ በሙሉ ኤች ዲ የሆነ የቴሌቪዥን ስርጭት በመጀመር ፈር ቀዳጅ መሆን ችሏል። ተቋሙ ከወራት የሙከራ ስርጭት በኋላ 2010 ጥር ወር ላይ በይፋ በኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾሙ የቴሌቪዥን ጣቢያውን በማስመረቅ በሙሉ አቅሙ በአማርኛ ቋንቋ ወደ ስርጭት ገብቷል።

ዘመኑ በሚጠይቀው የኦንላይ ሚዲያ ዘርፍም ራሱን በሰው ሀይል እና በቁሳቁስ በማስታጠቅ በአማርኛ፣ ኦሮሚኛ፣ ትግረኛ እና ኢንግሊዘኛ ቋንቋዎች በድረገፅ በኩል የዲጂታል ይዘትን በማሰራጨት ላይ ይገኛል። በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን በብዛት በሚጠቀሟቸው የፌስቡክ እና ትዊተር የማህብራዊ ትስስር ገፆች የዲጂታል ይዘትን በፅሁፍ፣ በፎቶግራፍ፣ በቪዲዮ እና በድምፅ በማቅረብ ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ በአማካይ በሳምንት እነዚህ የዘቶች ከ6 ሚሊየን የሚበልጥ ጎብኚን በመድረስ ላይ ይግኛሉ።

በሬደዮ ዘርፍም በብሄራዊ ስርጭትና ፋና ኤፍ ኤም 98 ነጥብ 1 በተጨማሪ በብሮድካስቲንግ ሚዲያ ልዩነት በመፍጠር በሀገራችን የሚዲያ ታሪክ በሚያስገርም ፍጥነት ከአዲስ አበባ ውጪ በ11 የክልል ከተሞች የኤፍ̣.ኤም ጣቢያችን የተሟላና በተደራጀ የሰው ሃይልና የሬድዮ ቴክኖሎጂ በማሟላት እርስ በራስ በማስተሳሰር ከፍቷል። በአሁኑ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ 12 የኤፍ̣.ኤም ጣቢያዎች ተቋቁመዋል። አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ አፋርኛ፣ ሶማሊኛ፣ ትግረኛ፣ ወላይትኛ እና ሲዳምኛ የስርጭት ቋንቋዎቹ ናቸው።የራሱን የቴክኖሎጂ፣ ጋዜጠኝነትና ኮሙዪኒኬሽን የስልጠና ማዕከልንም በማቋቋም የስልጠናና እና የማማከር አገልግሎት በመሰጥት ላይም ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በማዕከል እና በክልል በአጠቃላይ 1 ሺህ የባለቤትነት መንፈስና የህዝብ ወገንተኝነት ያላቸው ሰራተኞች አሉት።