Fana: At a Speed of Life!

ስልጣናቸውን በቀጣዩ ወር የሚለቁት የኒጀር ፕሬዚዳንት የ5 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሁለት ዙር የስልጣን ዘመን በኋላ ስልጣናቸውን በቀጣዩ ወር የሚለቁት የኒጀሩ ፕሬዚዳንት መሀመዱ የሱፍ የ2020 የአለም ትልቁን የመሪዎች ሽልማት አሸነፉ።

በዚህም በሱዳናዊው ቢሊየነር የተቋቋመውን የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ሽልማት በማሸነፋቸው 5 ሚሊየን ዶላር ይበረከትላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በአፍሪካ የመልካም አስተዳደር ለማሻሻል በ2006 የተቋቋመው ፋውንዴሽኑ የኒጀሩን ፕሬዚንዳንት ጨምሮ ስልጣናቸውን በሰለማዊ መንገድ ለቀቁ ስድስት የአፍሪካ መሪዎች ሽልማቱን ሰጥቷል።

የፋውንዴሽኑ ሊቀመንበር ሞጌይ ፕሬዚዳንቱ ሀገራቸው በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆናም ህዝባቸውን በለውጥ ጎዳና ወስደዋል ማለታቸውን ብሎበርግ አፍሪካ ዘግቧል።

ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው ይህ ሽልማት በኒጀር ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ዲሞክራሲን እና መልካም አስተዳደርን ለማስተዋወቅ እንዲሰሩ እንደሚያበረታታቸው ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.