Fana: At a Speed of Life!

ስኬታማ ሴቶች ለወጣት ሴቶች ልምድ የሚያካፍሉበት መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፈው አመት የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ስኬታማ ሴቶች ለወጣት ሴቶች ልምድ የሚያካፍሉበት መርሐ ግብር ይፋ ሆኗል፡፡

በሸራተን አዲስ ይፋ የሆነው መርሐ ግብር ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎችን ከስኬታማ ሴቶች ጋር በማጣመር በስልጠና ማብቃት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ሴት ሚኒስትሮች እና የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል።

ወጣት ሴቶችን ስኬታማ ከሆኑ እና ተምሳሌት መሆን ከሚችሉ ሴቶች ጋር በማገናኘት በተለያዩ ዘርፎች የአመራርነት ክህሎትን እንዲያሳድጉ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንዲያገኙ ማስቻል የፕሮግራሙ አላማ መሆኑ ተገልጿል።

የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መንግስት የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው የካቢኔውን 50 በመቶ ሴቶች እንዲይዙ ማድረግም የዚሁ ማሳያ ነው ብለዋል።

ይህን ስኬት ለማስቀጠል ሁሉም በዘርፉ ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ሊረባረቡ እንደሚገባም ገልጸዋል።

በተለያየ ዘርፍ ስኬታማ የሆኑና ወጣቶችን ለማብቃት ፈቃደኛ ለሆኑ እና ተምሳሌት ለመሆን ራሳቸውን ላዘጋጁትም ፕሬዚዳንቷ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፌልሰን አብዱላሂ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎችን በመምከርና በመደገፍ የሚደርስባቸውን ተጽዕኖ ተቋቁመው ወደ አመራርነት እንዲመጡ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

ወጣት ሴቶችን ስኬታማ ከሆኑ እና ተምሳሌት መሆን ከሚችሉ ሴቶች ጋር በማገናኘት በተለያዩ ዘርፎች የአመራርነት ክህሎትን እንዲያሳድጉ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንዲያገኙ ማስቻል የፕሮግራሙ አላማ መሆኑ ተገልጿል።

የተመረጡት ተማሪዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች ስኬታማ የሆኑ ሴቶች ልምዳቸውን እንደሚያካፍሏቸው የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

በቆንጅት ዘውዴ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.