Fana: At a Speed of Life!

ስድስት የሜዳ ቴኒስ መጫወቻ ኳሶችን አፉ ውስጥ በመያዝ ክብረ ወሰን ያስመዘገበው ውሻ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ ኒውዮርክ አንድ ውሻ ስድስት የሜዳ ቴኒስ መጫወቻ ኳሶችን በአንድ ጊዜ አፉ ውስጥ በመያዝ አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበ።

ፊኒሊ የተባለው የስድስት ዓመት ውሻ መጫወቻ ኳሶችን ያለምንም የሰው እርዳታ አፉ ውስጥ ማድረግ መቻሉ ተነግሯል።

የቴኒስ ኳሶችን የሚወደው ውሻ ከሁለት ዓመቱ ጀምሮ ቀስ በቀስ ኳሶችን በአፉ የመያዝ ልምድ እያዳበረ እንደመጣ አሳዳሪዎቹ ተናግረዋል።

ከሰሞኑም ስድስት ኳሶችን በአንድ ጊዜ አፉ ውስጥ በመያዝ አዲስ ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ችሏል።

ውሻው ይህን ሲያደርግ ምንም አይነት የሰው እርዳታ እንዳልተደረገለትም ነው የተነገረው።

አሳዳሪዎቹ የውሻውን ስም በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ (ጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርስ) ለማስፈር ያደረጉት ጥረት ግን ጊነስ ተጨማሪ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እፈልጋለሁ በማለቱ ለጊዜውም ቢሆን ሳይሳካ ቀርቷል።

ከዚህ በፊት በፈረንጆቹ 2003 በቴክሳስ የሚገኝ ውሻ አምስት ኳሶችን አፉ ውስጥ በመያዝ ክብረ ወሰን ማስመዝገቡ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ኦዲቲ ሴንትራል

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.