Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት ሳሙኤል ፍሬው በ3 ሺህ ሜትር መሰናከል የመጀመሪያውን ወርቅ ለሀገሩ አስገኘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ወንዶች አትሌት ሳሙኤል ፍሬው የመጀመሪያውን ወርቅ ለኢትዮጵያ አስገኝቷል፡፡ አትሌት ሳሙኤል ርቀቱን 8 ደቂቃ 24 ሰከንድ ከ30 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡ በመርሐ ግብሩ የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ውድድር ሲካሄድ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እንደሚጠበቁ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
Read More...

ኖቲንግሃም ፎረስት 4 ነጥብ ተቀነሰበት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኖቲንግሃም ፎረስት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን የፋይናንሺያል ጨዋነት ሕግ ተላልፏል በሚል አራት ነጥብ ተቀነሰበት፡፡ ቡድኑ ሕጉን በመተላለፍ ፕሪሚየር ሊጉ ትርፋማ እንዳይሆን ማድረጉም በገለልተኛ አጣሪ ተረጋግጧል ነው የተባለው፡፡ ይህን ተከትሎም ቡድኑ አራት ነጥብ ተቀንሶበት ነጥቡ ከ25 ወደ 21 ዝቅ ብሏል፡፡…

በቱርክ እግር ኳስ የሚስተዋሉ የሜዳ ላይ እረብሻዎች…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራብዞን ስፖርት ደጋፊዎች የፌነርባቼ ተጫዋቾችን በጨዋታው ማጠናቀቂያ መደባደባቸውን ተከትሎ የቱርክ ሱፐር ሊግ ሌላ አሳዛኝ ክስተት አስተናግዷል፡፡ ትላንት ምሽት በፓፓራ ፓርክ የተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክርን አስተናግዶ በፌነርባቼ 3 ለ 2 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡ በ87ኛው ደቂቃ ላይ የተለያዩ…

ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ስምንተኛ ሳምንት ጨዋታ በድሬዳዋ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡ ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና ቀን 10 ሰዓት ላይ ባደረጉት ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ በዚህም የፋሲል ከነማን ጎሎች…

አትሌት ጀማል ይመር የራሱን ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኮሪያ በተካሄደው የሴዑል ማራቶን አትሌት ጀማል ይመር የራሱን ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ አሸንፏል፡፡ አትሌት ጀማል ውድድሩን ያሸነፈው 2 ሰዓት ከ 6 ደቂቃ ከ8 ሰከንድ በመግባት ሲሆን÷ ይህም የግሉ ፈጣን ሠዓት ሆኖ ተመዝገቧል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ 18ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚሁ መሠረት 10:00 ሠዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከሲዳማ ቡና የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ እንዲሁም 1:00 ሠዓት ላይ ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ መድን ጨዋታቸውን እንደሚደርጉ የወጣው መርሐ-ግብር ያመላክታል፡፡

ከ15 ሺህ ሴቶች በላይ የተሳተፉበት የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ15 ሺህ ሴቶች በላይ የተሳተፉበት 21ኛ ዙር ቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ በውድድሩም ጉታኒ ሻንቆ 1ኛ፣ ብርነሽ ደሴ 2ኛ እና መቅደስ ሽመልስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡ መነሻ እና መድረሻውን አትላስ ሆቴል አካባቢ ያደረገው የሩጫ ውድድር÷ “የሴቶችን አቅም…