Fana: At a Speed of Life!

ስፔን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሰዓት እላፊ ገደብ ጣለች

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስፔን በሀገሪቱ ዳግም እያገረሸ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት በመላ ሀገሪቱ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሏ ተነግሯል።

በተጨማሪም ሀገሪቱ ብሄራዊ የጤና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇንም የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እንዳስታወቁት የምሽት የሰዓት እላፊ ገደቡ ከምሽቱ 5 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋት 12 ሰዓት ተፈፃሚ ይሆናል።

የሰዓት እላፊ ገደቡም ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ተፈፃሚ እንደሚደረግም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

እንዲሁም በጤና አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአየካባቢው የሚገኙ ባለስልጣናት በክልሎች መካከል የሚደረግ ጉዞን የመከልክል እርምጃን መውሰድ እንደሚችሉም አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በአንድ ስፍራ የሚሰበሰቡ ሰዎች ቁጥር ከ6 እንዳይበልጥ ክልከላ ሊጣል እንደሚችልም ተነግሯል።

አዲሱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና መመሪያው ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ የሀገሪቱ ምክር ቤት ክልከላው ለ6 ወራት እንዲያራዝመው እንደሚጠይቁም አስታውቀዋል።

ስፔን ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰውችም ሁለተኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በሀገሪቱ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን ተከትሎ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ይህንን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫም፥ አሁን ላይ ያለው የቫይረሱ ስርጭት አስጊ መሆኑን አስታውቅዋል።

ስፔን በመጀመሪያው ዙር የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ ጉዳት ከረሰባቸው ሀገራት ተርታ ተሰልፋ እንደነበረ አይዘነጋም።

አሁንም ልክ አንደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በሀገሪቱ በርካቶችን እያጠቃ እንደሚገኝ ተነግሯል።

በስፔን እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን የተሻገረ ሲሆን፥ 35 ሺህ ሰዎችንም በቫይረሱ ምክንያት አጥታለች።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.