Fana: At a Speed of Life!

ስፖርት ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረውና ራሱን እንዲችል የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ያደርጋል­- ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስፖርት ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው እና እራሱን ችሎ እንዲንቀሳቀስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የስፖርት ምክር ቤት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ምክትል ከንቲባ እና የስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፥ ስፖርት ለሰላም፣ ለጤና ፣ለማህበራዊ ትስስር እንዲሁም ለአንድነት ያለውን ሚና በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።

ስፖርት በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን ያስተዋወቀና ገፅታዋን የለወጠ በመሆኑ ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው እና እራሱን ችሎ እንዲንቀሳቀስ የከተማ አስተዳደሩ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልፀዋል።

ወጣቶች  ከአልባሌ ስፍራ ተቆጥበው በስፖርት ጤናቸውን እንዲጠብቁ በየአካባቢው ያሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲገነቡ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን በበኩላቸው ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ ለመመለስ ቀን ከሌት በመስራት ላደረጉት አስተዋጽኦ በስፖርት ቤተሰቡ ስም አመስግነዋል።

12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የስፖርት ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ የ2012 የምክር ቤቱ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የ2013 በጀት ዓመት እቅድ እና የስፖርታዊ ውድድሮች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መመሪያ ፕሮቶኮል ዙሪያ ሰፊ ውይይት በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክረተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.