Fana: At a Speed of Life!

ስፖርት በሀገሪቱ የብልፅግና ጉዞ ውስጥ ሁነኛ ቦታ ይዞ እንዲቀጥል ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፖርት በሀገሪቱ የብልፅግና ጉዞ ውስጥ ሁነኛ ቦታ ይዞ እንዲቀጥል ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ፡፡

የብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤት 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ በሸራተን አዲስ ተካሄዷል፡፡

ምክር ቤቱ በተለያዩ ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ በስፋት የተወያየ ሲሆን ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደመቀ መኮንን ኢትዮጵያ በመጪዎቹ ተከታታይ አመታት በሚሰራው ስራ የአፍሪካ ብልፅግና ተምሳሌት ሆና እንድትቀጥል የ10 ዓመት መሪ ሀሳብ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል ፡፡

የስፖርት መርሆዎችም በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ምንአልባትም ከየትኛውም ተቋም በላይ በ10 ዓመት መሪ የልማት ሀሳብ ውስጥ ተንፀባርቋልም ነው ያሉት፡፡

ስፖርት ከብልፅግና፣ ከአብሮነት፣ ከወንድማማችነት እና ጤናማ ማህበረሰብ ከመገንባት አኳያ ያለው መስተጋብር ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ይህን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ትልቅ ኃላፊነት ተጥሎብናልም ብለዋል ባደረጉት ንግግር፡፡

በመሆኑም ስፖርት በሀገሪቱ የብልፅግና ጉዞ ውስጥ ሁነኛ ቦታ ይዞ እንዲቀጥል ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ማለታቸውን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር በበኩላቸው የስፖርት ውጤታማነትን ለማጎልበት በየደረጃው ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው የህብረተቡ በስፖርቱ የመሳተፍና የመጠቀም ፍላጎት በሚገባ ማሟላት እንዳልተቻለ ገልፀዋል።

ለዚህም በአደረጃጀት፣ በአሰራር፣ በማስፈጸም አቅም ደረጃ የሚታዩ ችግሮች ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በመሆኑምይህን ችግር ለመቅረፍ በሀገራዊ የለውጥ ጉዞ የተቃኘ ሀገራዊ የስፖርት ሪፎርም ፕሮግራም ተዘጋጅቶ በየደረጃው በማወያየት ወደ ትግበራ ምዕራፍ መገባቱንም አንስተዋል፡፡

“ስፖርት ለሁሉም ፤ ሁሉም ለስፖርት” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ስብሰባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.