Fana: At a Speed of Life!

ሶማሊያ 200 ሺህ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ተረከበች

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ሶማሊያ 200 ሺህ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ከቻይና ተረከበች፡፡
ሲኖፋርማ የተባለውን ይህን ክትባት የሶማሊያ የጤና ሚኒስትር ፋውዝያ አቢካር በሶማሊያ ከቻይና አምባሳደር ኪን ጂያን ተረክበዋል ፡፡
ሶማሊያ ባለፈው ወር ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት ድጋፍ ሰጪ ተቋም በመጀመሪያ ዙር 300 ሺህ ክትባት ተቀብላለች ፡፡
እስካሁን በሶማሊያ 12 ሺህ 406 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 618 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለንⵑ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.