Fana: At a Speed of Life!

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ በመደመር መፅሃፍ ገቢ የሚገነቡ ትምህርት ቤቶችን የመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጥ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ በመደመር መፅሃፍ ገቢ የሚገነቡ የሁለተኛ ዙር ትምህርት ቤቶችን የመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጥ ጀመሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመደመር መፅሃፍ ገቢ ትምህርት ቤቶች በሌሉባቸው አካባቢዎች የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት እንዲገነባ ገቢውን  ማስገባታቸው ይታወሳል።

በመሆኑም ክልሎች መፅሃፉን ሸጠው ካስገቡት ገንዘብ ትምህርት ቤቶችን እንዲገነቡ ቃል በተገባላቸው መሰረት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን ሲራሮ ወረዳ ሮፒ ከተማ ለሚገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሁለተኛ ዙር የትምህርት ቤቶች ግንባታ የመጀመሪያው መሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል።

በስነ ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ፣ አባገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

በፍሬህይወት ሰፊው

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.