Fana: At a Speed of Life!

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ወረዳ ለሚገነባው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አኖሩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ወረዳ ለሚገነባው ለኢፋ ቦሩ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አኖሩ።

ከመደመር መጽሀፍ ገቢ የሚገነባዉ ሁለተኛ ዙር ትምህርት ቤት ግንባታ ሁለተኛዉ የመሰረት ድንጋይ በአምቦ የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን የትውልድ ስፍራ በሆነችው ቦሩ ጎረምቲ ቀበሌ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል ።

ለትምህርት ቤት ግንባታውም  14 ሚሊየን ብር  መመደቡም ነው የተለጸው።

16 ክፍሎች የሚኖሩት ትምህርት ቤቱ በዉስጡ የአስተዳደር ህንጻ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ላቦራቶሪ፣ የቤተ መጽሀፍ የኮምፕዩተር ላብራቶሪ እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ክፍሎችን ማካተቱም ነው የተነገረው።

የትምህርት ቤቱ የመሰረተ ድንጋይ  ማኖር መርሃ ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ  ሃላፊዎች መገኘታቸውን ከቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.